|
የራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ የስነምግባር መርሆ አባላቱ ተገዢ የሚሆኑበት መመሪያ ነው፡፡ መመሪያዎችም የሚከተሉት ናቸው
- እርስ በራሳችንም ሆነ ከሌሎች ጋር የሚኖረን የሥራ ግንኙነት ግልጽነት፣ ተጠያቂነት እና ሐቀኝነት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም ተግባራችንም ከጉቦ፣ ከሙስና እና አግባብ ከሌለው በስልጣን ወይም ባለን አብላጫ አቅም ከመጠቀም የተቆጠበ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተግባራችንን ስንፈጽም ሕጋዊ፣ ሙያዊ ሰነ-ምግባርና ሰብአዊ ገደቦችን ማክበር ብቻ ሳይሆን ከኀብርተሰቡ አመኔታና ክብር የሚያገኝ ሊሆን ይገባል፡፡
- ማንኛውም ማኀበራዊ ሥራችን በዴሞክራስያዊ መርህ ላይ የተመሠረተ ሆኖ በተለይም ትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያን ወክለን የምንወስደው እርምጃ የፖለቲካም ሆነ የተለየ እምነት ወገናዊ ሊሆን አይገባም፡፡
- በማንኛውም ቦታና ጊዜ ጉቦን፣ ሙስናን እና በስልጣን መባለግን በግልጽ ስናይ በትጋትና በመንፈስ ቆራጥነት መቃወም አለብን፡፡
- ጉቦን፣ ሙስናን እና በስልጣን መባለግን መቃወምና ማጋለጥ የምንችለው በተጨባጭ ጥናታዊ መረጃ ላይ በመደገፍ ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ተግባር 㗹የትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ አመራር አካላት በሚያደርጉት ጥረት ሁሉ አባላት የመሳተፍ መብትም ግዴታም አለባቸው፡፡
- ለትራንስፓረንሲ ኢትዮጵያ አመራር አካል የምትወዳደር/ የሚወዳደር እጩ በጊዜው ያላት/ያለው የፖለቲካም ሆነ ማንኛውም አቋም ከማኀበሩ አላማ ጋር የማይፃረር መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባት/አለበት፡፡
|